መንግስት በጥፋት ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል


የካቲት 15፣ 2008 – ጠቅላይ ሚንስትሩ በሁለት አብይ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም በመግለጫቸው እንዳሉት የፌደራል ስርአቱ የፈጠረውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በአንዳንድ ኦሮሚያ አካባቢዎች ተገቢ ጥያቄ መነሳቱን ጠቁመዋል፡፡

መንግስትም እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ሆኖም በሻዕቢያ መንግስትና በውጭ ሃይሎች ድጋፍ በኦሮሚያ በአንዳንድ አካባቢዎች በመንግስትና በህዝብ ንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

መንግስትና ህዝቡ ዋነኛ ተዋናይነት በጋራ በመተባበር ችግሩን ለመፍታት ያደረጉት ስራ ውጤታማ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ተናግረዋል፡፡

መንግስት የእነዚህን የጥፋት ሃይሎችን ቀቢጸ ተስፋ ለመከላከል የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚስትር ኃይለማርያም ከኤልኒኖ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ እንዳሉት እስካሁን አንድም የሠው ህይወት አለመጥፋቱን አረጋግጠዋል፡፡

የሀገሪቱን የህዳሴ ጉዞ በማያስተጓጉል መልኩ ድርቁን ለመቆጣጠር የተጀመሩ ጥረቶች መቀጠላቸውንም አብራርተዋል፡፡

EBC

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.