በአዲስ አበባ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ በሙስና የተጠረጠሩ ግለሰቦች አሁንም በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው::

Addis Ababa city view

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2008 – በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች አሁንም በቁጥጥር ስር እየዋሉ ፍርድ ቤት እየቀረቡ ነው።

በዛሬው እለት ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሁለት ፈጻሚዎች እዳ እና እግድ ያለበትን ይዞታ እንደሌለበት በማስመሰል ለሶስተኛ ወገን እንዲሸጥ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በክፍለ ከተማቸው በሚገኝ ህንፃ ያረፈበት ቦታ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የግብር እዳ ያለበት መሆኑ እየታወቀ እና ቦታው እግዳ የተጣለበት እንደሆነ በሰነድ ተደግፎ የተቀመጠ ሆኖ ሳለ ከሌሎች 9 ግለሰቦች ጋር በመሆን ከእዳ ነፃ እንደሆነ በማድረግ ለሶስተኛ ወገን እንዲተላለፍ አድርገዋል ነው የተባለው።

አቃቤ ህግ በምርመራ ያገኘሁት ነው ባለው በዚህ መረጃ ምስክርና ሰነድ ማሰባሰብ ስራ መስራቱን ገልጾ ሌሎች ማስረጃዎችን ለማሰባሰብና ቀሪ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የወንጀል ችሎትም ለመጋቢት 8 2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ እስካሁን ከ100 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው አብዛኞቹ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*