በአዲስ አበባ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው መንገዶች ተመረቁ::

Addis Ababa

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተገነቡ የአስፋልት መንገዶችን አስመረቀ።

መንገዶቹ 16 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ሲሆን፥ በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ያቃልላሉ ተብሏል።

በዛሬው እለት የተመረቁት መንገዶች፦

1. ከአስኮ አዲሱ ሰፈር እስከ ፊሊጶስ ሎሚ ሜዳ የሚደርሰው መንገድ – 3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር

2. ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል እስከ ቂሊንጦ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ – 3 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር

3. ከመስቀል ፍላወር – ጎርጎሪዮስ – ቦሌ ሚካኤል (1 ነጥብ 45 ኪሎ ሜትር)

4. ከቀድሞው ሶስት ቁጥር ማዞሪያ – ዘንአ ድልድይ – ታቦት ማደሪያ (1 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር)

5. የረር ሆቴል – ካራ መንገድ – ኮተቤ 02 (0 ነጥብ 92 ኪሌ ሜትር)

6. ከቅዱስ ዮሴፍ አደባባይ እስከ ደብረ ዘይት መንገድ – 0 ነጥብ 36 ኪሎ ሜትር

ከደጃች ውቤ – አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ – አትክልት ተራ – አውቶብስ ተራ (2 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር) እንዲሁም በሰባተኛ እስከ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተገነባው የ2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መንገድም ከስአት በኋላ እንደሚመረቁ ተገልጿል።

መንገዶቹ በተገነቡባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የተገነቡ የመንገድ ፕሮጀክቶች የትራፊክ ፍሰቱን የተሻለ ከማድረግም ባሻገር የከተማዋን ገጽታ የሚለውጡ ናቸው ብለዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.