አዲሱ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ከሀምሌ 1 ጀምሮ በተገኘ ገቢ ላይ ተፈፃሚ እንዲሆን ተወሰነ::

Tax symbol

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲሱን የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ አፀደቀ። ምክር ቤቱ ከሰዓታት በፊት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የገቢ ግብር ማሻሻያው ከሀምሌ 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ወስኗል።

ከገቢ ግብር አዋጁ በተጨማሪ የታክስ አስተዳደር አዋጅ እና የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጆችም በአስቸኳይ ስብሰባው ፀድቀዋል።

ምክር ቤቱ በረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ ላይ የተለያዩ ማስተካከያዎችንም ያደረገ ሲሆን፥ በዚህም የታክስ አስተዳደር አዋጅ የሚለው ስያሜ የፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ እንዲባልም ምክር ቤቱ ማሻሻያ አድርጎበታል።

ከታክስ ጋር በተያያዘ ቅሬታ በማቅረብ ምላሽ እና ለመስጠት የተያዘው የ120 ቀናት ጊዜም ወደ 180 እንዲራዘም ማሻሻያ ተደርጎበታል።

እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ሳይመዘገብ ደረሰኝ የሰጠ ሰውን በተመለከተም ግለሰቡ በሰጠው ገንዘብ እጥፍ እንዲከፍል የሚለውም በብር 50 ሺህ እንዲስተካከል ተደርጓል።

በዚህ መሰረትም ይህንን ወንጀል የፈፀመ ማንኛውም ግለሰብ የ50 ሺህ ብር መቀጮ የሚጣልበት ይሆናል።

ምክር ቤቱ በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባው የቀረቡለትን 16 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት በሙሉ ድመጽ አጽድቋል።

የተሾሙት ዳኞችም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪ የጂኦተርማል ሃብት ልማት ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የተዘጋጀውን አዋጅም አፅድቋል።

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*