አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመካንነት ህክምና ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው::

black lion hospital

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2008 – በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመካንነት ህክምና ትምህርት ሊሰጥ ነው።

ትምህርቱ የፊታችን ሰኞ ይጀመራል ተብሏል።

የትምህርቱ መጀመር ህክምናውን ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገራት የሚደረገውን ጉዞ እንደሚያስቀር ተነግሯል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምክትል ፕሮፌሰር ማእረግ የማህፀንና የፅንስ ህክምና ትምህርት ክፍል ሃላፊ ዶክተር እስክንድር ከበደ፥ በትምህርቱ መጀመር ታካሚዎች በቀላሉ ህክምናውን ማግኘት እንደሚያስችል ገልፀዋል።

ትምህርቱ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል።

የፊታችን ሰኞ የሚጀመረውን የመካንንት ትምህርት አስመልክቶም በዛሬው እለት በጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ይፋዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*