ኢትዮጵያ እና ሱዳን በፀጥታ ዙሪያ በአዲስ አበባ እየመከሩ ነው::

Soldiers

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በቀጠናው የሚታዩ የሰላም እና ፀጥታ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እየሰሩ መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ዘርፍ አመራሮች በሀገራቱ እና በቀጠናዊ ሰላም እና ፀጥታ ሁኔታ በአዲስ አበባ መምከር ጀምረዋል፡፡

አመራሮቹ በባለፈው ዓመት በሱዳን ካርቱም ተመሳሳይ ውይይት ማካሄዳቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ በዚህም ሀገራቱ በአካባቢያዊ እና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ራሳቸውን ለማብቃት የተሞክሮ ልውውጥ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡

የመከላከያ አመራሮቹ በአዲስ አበባ ውይይታቸውም በሰላም ማስከበር፣ ሽብርተኝነትን በመዋጋት፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ረገድ የመጡ ለውጦችንና ቀሪ ስራዎችን ይገመግማሉ ተብሏል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያና ሱዳን የመከላከያ ሚኒስትሮች ዲፕሎማሳዊ ግንኙነት የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማጠናክር እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች እንዲተሳሰሩ ከማድረግ አኳያ ያመጣው ውጤት እንደሚዳሰስም አቶ ሲራጅ ገልጸዋል፡፡

የሱዳን የመከላከያ አመራሮች ልዑክ መሪ ሌተናል ጀኔራል ኢልሳር ሁሴን ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ በትብብር መስራቷ ሁሌም የምትኮራበት ነው ብለዋል፡፡

ሀገራቸው ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማስቀጠል እና በቀጠናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሰላም እና ጸጥታ ዘርፍ በጋራ ለመስራት እ.አ.አበ2009 የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡

EBC

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.