የተሻሻለው የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ይፋ ሆነ::

Pie Chart

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የተሻሻለውን የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ይፋ አደረገ። የሚኒስቴሩ የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዋሲሁን አባተ፥ ረቂቅ አዋጁ ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻሻለ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ረቂቅ አዋጁ ተቀጣሪ ሰራተኞች አሁን እየከፈሉት ያለውን የገቢ ግብር መጠን እንዲቀንስ የሚያደርግና፥ የህብረተሰቡን ገቢ ከግምት ያስገባ የገቢ ግብር ምጣኔ፣ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ተብሎ የተቀመጠውን የደመዎዝ የግብር ጣሪያን የሚያሻሽልም ነው።

በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ደመዎዛቸው ከ6 መቶ ብር በታች የሆነ ተቀጣሪ ሰራተኞች ግብር አይከፍሉም።

ረቂቅ አዋጁ እንዲሻሻል የተደረገው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከደረሰበት ደረጃ አንፃር ዝቅተኛው ወርሃዊ ደመወዝ በማደጉ እና ከጊዜው እና የዜጎች ገቢ ጋር የተመጣጠነ የግብር ስርአት ለመዘርጋት መሆኑንም አስረድተዋል።

ሌላው በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ የተካተተው የግብር አይነት የንግድ ግብር ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ከግብር ነፃ የነበረውን 1 ሺህ 8 መቶ ብር ወደ 7 ሺህ አሳድጎታል።

በዚህ መሰረትም በዓመት 7 ሺህ ብር የኪራይ ገቢ ከግብር ነጻ በመሆን ከዛ በላይ ባለው ላይ ብቻ ግብር ይከፈልበታል።

አንድ ነጋዴ በተተመነበት ግብር ላይ ቅሬታ ቢኖረው፥ የፍሬ ግብሩን፣ መቀጮው እና ወለዱ ታሳቢ ተደርጎ የጠቅላላ ክፍያውን 50 በመቶ በማስያዝ ይግባኝ የሚልበት አሰራርም በረቂቅ አዋጁ ተቀይሯል።

ረቂቁ የግብር ይግባኝን የሚሰማ ራሱን የቻለ ተቋም እንዲቋቋምና የግብር ህግ የሚያዩ የተለያዩ ትርጎሞችን የሚያስቀር አሰራር እንዲፈጠርም ያስገድዳል።

በመጭው ሃሙስ እና ዓርብም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከውጭ ሃገር ኩባንያዎች እና ከሙያ ማህበራት ጋር ውይይት ይደረግበታልም ነው ያሉት አቶ ዋሲሁን።

በውይይት ዳብሮ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀረበ በኋላም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ፥ ከሃምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ፀድቆ ስራ ላይ እንዲውል እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በዚህም መሰረት ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ለሚጣለው ግብር ተፈጻሚ የሚሆኑትን ምጣኔዎች በሚከተለው መልኩ አስቀምጧል፤

Read More

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.