የኢድ አልፈጥር በአል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም መከበሩን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

Ethiopian Federal Police Head office

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 10 ፣ 2007 – የኢድ አልፈጥር በአል ያለምንም የጸጥታ ችግር በመላ ሃገሪቱ በሰላም መከበሩን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል አሰፋ አብዩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አንደተናገሩት ህዝበ ሙስሊሙ ከወትሮው በተለየ በብዛት በተለመዱ ስፍራዎች በመውጣት ሃይማኖቱ የሚያዘውን ስርአት ፈጽሞ በሰላም ወደየቤቱ ተመልሷል።

በሌላ በኩል 3ኛው የፋይናንስ ለልማት አለም አቀፍ ጉባኤ ያለምንም ጸጥታ ችግር በሰላም የተጠናቀቀ መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራሉ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ የጸጥታ አካላቱ ለዚህ ስኬት ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋልም ብለዋል።

በተለይም ህብረተሰቡ እንግዶች በሚያልፉባቸው አካባቢዎች በሚዘጉ መንገዶች የሚደርስበትን እንግልት ከምንም ሳይቆጥር ያሳየውን ትእግስት ጨምሮ፤ የሚጠረጥራቸው እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት ለጸጥታ ሃይሉ እስከ መጠቆም ላሳየው አስተዋጽኦ አድናቆት ሊቸረው ይገባል ብለዋል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*