ጠጥተው የሚያሽከረክሩ ግለሰቦችን የሚቆጣጠረው መሳሪያ በአዲስ አበባ በሃምሌ ወር ስራ ላይ ይውላል::

Alcohol Tester

አልኮል ጠጥተው የሚያሽከረክሩ ግለሰቦችን መቆጣጠር የሚያስችለው መሳሪያ ከቀጣዩ ወር ጀምሮ ስራ ላይ እንደሚውል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናገረ።

በኮሚሽኑ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ግርማ ተሰማ እንዳሉት፥ ከሃምሌ ጀምሮ ተደጋጋሚ አደጋ በሚደርስባቸውና በተለዩ ቦታዎች በመሳሪያው በመታገዝ የቁጥጥርና ክትትል ስራው ይጀመራል፡፡

የአልኮል መጠጥ መመርመሪያ እንዲሁም የፍጥነት /ራዳር / መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ግዥ መፈፀሙንም ገልጸዋል።

መሳሪያው በተለይም በሌሊት አልኮል ጠጥተውና ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ የሚያሽከረክሩ ግለሰቦችን ለመቆጣጠርና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋል ነው ያሉት።

ለዚሁ ተግባር ውጤታማነት በሶስት ፈረቃ የ24 ሰዓት የቁጥጥር ሥራ እንደሚጀመርም ተናግረዋል። ወደ ተግባር ከመገባቱ አስቀድሞ ስለመሳሪያዎቹ አጠቃቀም ሥልጠና እየተሰጠ ነው ተብሏል።

መንጃ ፍቃድ ሳይኖራቸው በሌሊት የሚያሽከርክሩ ግለሰቦች ላይም ቁጥጥሩ ይደረጋል።

ኤፍ ቢ ሲ

Share this on:

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


*

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.